በቤት ውስጥ እስር ላይ የነበሩት ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ ታዩ

ህዳር 08፣2010

ላለፉት ሶስት ቀናት በቤት ውስጥ እስር ላይ የነበሩት የዝምባቡዌው ፕሬዝዳንት ሮበርት  ሙጋቤ  በአንድ ዩኒቨርሲቲ  የምርቃት ስነ ስርአት ላይ  መገኘታቸው ተገልጿል፡፡

የአገሪቱ ጦር በፕሬዝዳንቱና በምክትላቸው መካከል አለመግባባት መከሰቱን ተክተሎ የዝምባቡዌ ጦር የአገሪቱን ካለፈው ሮቡዕ ጀምሮ ተቆጣጥሮ ይገኛል፡፡

የዝምባቡዌ ገዥው ፓርቲ ዛኑ ፒኤፍ  በዛሬው ዕለት ፕሬዝዳንት ሙጋቤን ከኃላፊነታቸው ለማስወገድ በሚያስችለው ምከረ ሀሳብ  ላይ እየመከረ መሆኑም ተሰምቷል፡፡ፓርቲያቻው የሚያቀርበውን የስልጣን ልቀቁ ጥያቄ ፕሬዝዳንት ሙጋቤ  በፀጋ የማይቀበሉ ከሆነ በሚቀጥለው ሳምንት  በህግ አግባብ ከስልጣናቸው ሊነሱ የሚችሉበትን አግባብም ይቀይሳል ተብሎ ይጠበቃል ብሏል ሲጂቲኤን የፓርቲውን የውስጥ ምንጮች ዋቢ በማድርግ ባቀረበው ዘገባ፡፡

ደቡብ  አፍሪካ በምትመራው ሽምግልና ፕሬዝዳንት ሙጋቤ ከስልጠናቸው እንዲወርዱ ቢጠየቁም አሻፈረኝ ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

ብዙዎች በዝምባቡዌ የተፈጠረው ሁኔታ በቅርብ እያጤኑት መሆኑንም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡