በሊቢያ በስደተኞች ላይ “የባርያ ንግድ” ሲከናወን የሚያሳይ ምስል መታየቱ ቁጣ አስነስቷል

ህዳር 10፣2010

በሊቢያ አፍሪካዊያን ስደተኞች ላይ  "የባርያ ንግድ" ሲከናወን የሚያሳይ ምስል መታየቱ የአፍሪካ ህብረትን ክፉኛ አስቆጥቷል፡፡

አፍሪካዊያን ስደተኞች በሊቢያ ለግብርና ስራ እንዲያገለግሉ በዚህ ሳምንት ሲኤንኤን ላይ ለጨረታ ሲቀርቡ የሚያሳይ ምስል መለቀቁን ተከትሎ ነው ህብረቱን ክፉኛ ያስቀጣው፡

የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበር  የጊኒው ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴ በዚህ ዘመን ላይ መታት የሌለበት ድርጊት በመሆኑ የድርጊቱ ፈፃዎችን ለህግ ማቅርብ ጊዜ ሊሰጠው እንደማይገባ ተናግረዋል፡፡

አፍሪካዊያን ስደተኞች በሊቢያ አድርገው ወደ አውሮፓ ለመግባት በሚያደርጉት ጥረት በህገወጥ ሰው አዘዋዋሪች ሲወድቁ ለጉልበት ብዝበዛ እየተዳረጉ መሆኑ መነገር ከተጀመረ ሰንበትበት ብሏል፡፡

በሊቢያ "የባርያ መገበያያ" አንድ አፍሪካዊ ስደተኛ በ400 ዶላር ሲሸጥ መታየቱ ብዙዎችን ያሳዘነ ድርጊት ሆኗል፡፡

ፕሬዝዳንት ኮንዴ እንዲህ መሰል አይነት ዘመናዊ ባርነት ማብቃት አለበት፣አፍሪካ ህብረትም ድርጊቱን ከስሩ ለማስውገድ ያሉ አማራጮችን ሁሉ እንደሚጠቀም አስገንዝበዋል፡፡

ይሁን እንጂ ሊቢያ ድርጊቱ ስለ መፈፀም አለመፈፀሙ ምርምራ እያደረገች መሆኗም ተዘግቧል፡፡

ባለፈው ሚያዚያ ግን አለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት በሊቢያ በስደተኞች ላይ የባርያ ፍንገላ እንተከናወነ ስለመሆኑ  በተጨባጭ ማስረጃዎች ረጋጡን ገልፆ ነበር፡፡

ምንጭ፡‑ ቢቢሲ