ኢትዮጵያን የሚጎበኙ ቻይናዉያን ቱሪስቶች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል:- ሚኒስቴሩ

ህዳር 12፣2010

ኢትዮጵያን የሚጎበኙ ቻይናዉያን ቱሪስቶች ቁጥር ባለፉት አመታት እየጨመረ መምጣቱን  የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል᎓᎓

በሚኒስቴሩ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ካሳሁን አያሌው እንደገለጹት በ2006 ዓ.ም 41 ሺህ 660 የቻይና ቱሪስቶች ኢትዮጵያውያን የጎበኙ ሲሆን በ2002 ዓ.ም ከነበረው 35 ሺህ 383 ከ6 ሺህ በላይብ ልጫ አለው᎓᎓

የያዝነው የሩብ አመቱን ሪፖርት ስንመለከትም የቱሪስት ፍሰቱ ከባለፈው አመት ጋር  ሲነጻጸር   ጭማሪ እንዳለው ያሳያል ብለዋል᎓᎓

የአፍሪካ አገራት እና የቻይና ቱሪስቶች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን የገለጹት ባለሞያው የጎረቤት አገራት ኬንያ ጂቡቲና የኤርትራ ዜጎችም ለጉብኝት እንደሚመጡ መረዳት ይቻላል ብለዋል᎓᎓

አሁንም ቢሆን ኢትዮጵያን በብዛት የሚጎበኙ የአሜሪካ ቱሪስቶቸ ናቸው᎓᎓ ግን ወደ አገራችን ለጉብኝት የማይመጡ የነበሩ ቱሪስቶች ቁጥርም እየጨመረ መምጣቱንም አቶ ካሳሁን አመልክተዋል።

ቻይናውያን  ላለፉት 10 እና  15 አመታት  በኢንቨስትመንት ነበር ወደ ሃገራችን የሚገቡት᎓᎓ አሁን ግን ቻይናዎች ቱሪዝሙን እየተቀላቀሉ ነው᎓᎓

ከአውሮፓውያኑ 2013 ከ15 ሺህ ተነስቶ አሁን ላይ 44 ሺህ ቻይናውያን ቱሪስቶች ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል᎓᎓

በአለፉት 3 ወራት 256 ሺህ የውጭ አገር ዜጎች ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል። 950 ሚሊዮን ዶላር ገቢም ተገኝቷል᎓᎓ ይህ አሃዝ ከአምናው ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ9ነጥብ 9 ከመቶ ብልጫ አለው ተብሏል᎓᎓

መቶ ሚሊዮን የቻይና ቱሪስቶች አሉ ተብሎ ይገመታል ᎓᎓ ከነዚህ ውስጥ አንድ ሚሊዮኑን ወደ አፍሪካ ለማምጣት ታቅዶ በኢትዮጵያ በኩል 44ሺህ መድረሱን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በመስፍን ገብረማርያም