ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለቀቁ

የዚምባብዌው ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ስልጣናቸው በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን የአገሪቱ ፓርላማ ገለጸ፡፡

ዚመባብዌን ለ37 አመታት የመሩት የ93 አመቱ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ  ለአገሪቱ ፓርላማ በላኩት ደብዳቤ ውሳኔያቸው ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ለማደረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የፕሬዝዳንቱን ስልጣን መልቀቅ ተከትሎ ዚምባብዌውያን በመንገዶች ላይ ወጥተው ደስታቸው  እየገለፁ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡