ኢትዮጵያ ባለፉት በጥራጥሬና ቅባት እህሎች እድገት እያሳች እንደምትገኝ ተገለፀ

ህዳር 14፣2010

ኢትዮጵያ ባለፉት አሥር ዓመታት በጥራጥሬና ቅባት እህሎች እድገት እያሳች እንደምትገኝ ተገለፀ፡፡

ሰባተኛው ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና የቅባትና ቅመማ ቅመም ጉባኤ በአዲስ አበባ ተጀምሯል፡፡

በጉባኤው መክፈቻ የ2ዐዐ9 በጀት ዓመት በውጭ ንግድ የተሻለ የውጭ ምንዛሪ ላስገኙ ኩባንያዎችም የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በዘርፉ በመጠንና በገቢ ደረጃ ከፍተኛ መሻሻሎች መታየታቸውን ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ተናግረዋል፡፡

የንግድ ሚንስትሩ ዶክተር በቀለ ቡላዶ ሀገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘውን ጥቅም ለማሳደግ በአርሶ አደሩና በላኪው ዙያ ቀጣይ ሥራዎች ይጠበቃሉ ብለዋል፡፡

በዚህ ጉባኤ ከ2ዐ ሀገራት የመጡ በዘርፉ የተሰማሩ ባሀለሀብቶችና ከ25ዐ በላይ የሀገር ውስጥ ላኪዎች ተሳታፊዎች ናቸው፡፡