መገናኛ ብዙሀን ምክንያታዊ ህብረተሰብ እንዲፈጠር መስራት ይገባቸዋል:- መንግስት

ህዳር 14፣2010

መገናኛ ብዙሃን በየደረጃዉ ያሉ የኮሚኒኬሽን መዋቅሮች ትክክለኛና ወቅታዊ  መረጃን በማሰራጨት ምክንያታዊ ህብረተሰብ እንዲፈጠር መስራት ቀዳሚ ተግባራቸዉ ሊሆን እንደሚገባ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ገለጸ፡፡

ሀገር አቀፍ የመገናኛ ብሁሃንና ኮሚዩኒኬሽን የጋራ መድረክ ትናንት በሃዋሳ ከተማ ተጀምሯል፡፡

በመድረኩ ላይ የጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚንስትሩ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ መገናኛ ብዙሃንና የኮሚዩኒኬሽን ዘርፉ በሃገሪቱ እየተከናወኑ ያሉትን የሰላም፣ የልማትና የዲሞክራሲ ግንባታ ስራወችን በማጠናከር በኩል ጉልህ ሚና ተጫዉቷል ብለዋል፡፡

በመገናኛ ብዙሃንና የኮሚኒኬሽን ዘርፉ አማካኝነት በተሰሩ ተግባራትም በሃገሪቱ ዋና ዋና ጉዳዮች ዙሪያ ብሄራዊ መግባባት እያደገ መምጣቱን ነዉ ዶ/ር ነገሪ የገለጹት፡፡

ነገር ግን በሃገሪቱ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲረጋገጥ በማድረግ ረገድ መገናኛ ብሁሃን ብዙ ስራዎች መስራት እንዳለባቸዉም በመድረኩ ተጠቁሟል፡፡

በሃዋሳ እየተካሄደ ያለዉ ይህ መድረክ ለቀጣይ ሶስት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን በተለያዩ ጉዳዮች ላይም ይመክራል ተብሏል፡፡

ዘገባዉ የኢዜአ ነዉ፡፡