አሜሪካ በአልሸባብ ታጣቂዎች ላይ የፈጸመችው የአየር ጥቃት በጠየቀችው መሰረት መሆኑን ሶማሊያ ገለጸች

ህዳር 14፣2010

ሶማሊያ 100 የአልሸባብ ታጣቂዎች የሞቱበት  የአሜሪካን የአየር ጥቃት የተካሄደው እኔ በጠየቅኩት መሰረት ነው አለች᎓᎓

አሜሪካ ሕዳር 12/2010 ዓ.ም በአልሸባብ ላይ በሰው አልባ አውሮፕላን የፈጸመችው የአየር ጥቃት በሶማሊያ መንግስት ጥያቄ መሰረት መሆኑ ተገልጿል።

ታጣቂዎቹ  ፈንጂዎችበማዘጋጀት ጥቃቶችንለመፈጸም በዝግጅት ላይእንደነበሩም  ሶማሊያ አስታውቃለች።

በታጣቂዎቹ  ላይየሚደረገውጥቃት ተጠናክሮ  እንደሚቀጥልም ገልጻለች።

በጥቃቱ 100 የአልሸባብ ታጣቂዎች መገደላቸው ይታወሳል።

ጥቃቱ የተፈጸመው ከዋና ከተማዋ ሞቃድሾ ሰሜና ምዕራብ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት በሚገኘው በአልሸባብ ማስልጠኛ ካምፕ መሆኑንም ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል።