ኢትዮጵያ ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ከሱዳንና ግብፅ ጋር ተባብራ መስራትዋን እንደምትቀጥል አስታወቀች

ህዳር 14፡2010

ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ከሱዳንና ግብፅ ጋር ተባብራ መስራትዋን እንደምትቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የህዳሴውን ግድብ አስመልክቶ በግብፅ በኩል እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ የሶስቱ ሀገራት መሪዎች የፈረሙትን መርሆዎች የሚጥስ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ተናግረዋል፡፡

ትክክለኛው መፍትሄ ሁሉንም የአባይ ተፋሰስ ሀገራት ተጠቃሚ የሚያደርግ ስርአት መዘርጋት መሆኑንም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል፡፡