በአዲስ አበባ የማህበራዊ አቀፍ የጤና መድህን ይፋ ሆነ

ህዳር 19፣2010

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቀጣዩ ወር ታህሳስ ሁለት  የሚጀምር የማህበራዊ አቀፍ የጤና መድህን በምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታዉ ይፋ ሆነ ።

የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን በከተማዋ ዉስጥ በተለዩ ዘጠኝ ወረዳዎች ላይ በሙከራ ደረጃ ሊተገበር መሆኑን ምክትል ከንቲባዉ ተናግረዋል  ።

የፕሮግራሙ መጀመር የህብረተሰቡን የጤና ተደራሽነት ለማሳደግና የጤና ተቁማቱን አቅም ለማጎልበት ይረዳል ብለዋል ።

ለመርሃ ግብሩ ስኬታማነትም የከተማዋ አመራር ርብርብ እንዲያደርግ አቶ አባተ ጥሪ አቅርበዋል ።