ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መቋቋሚያ ቃል ከተገባው ከ10 በመቶ በታች ነው እየተለቀቀ ያለው ፡‑ ጥናቶች

የካቲት 29 ፣ 2009

ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መቋቋሚያ ቃል ከተገባው ውስጥ ለፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ እየተለቀቀ ያለው ከ10 በመቶ በታች መሆኑን ተመራማሪዎች ገለፁ፡፡

የፋይናስ ተመራማሪዎች ይፋ ባረጉት ጥናት አለም አቀፉ  ማህበረሰብ  በተለይም በአየር ንብረት ለውጥ የተጎዱ ታዳጊ አገራት ችግሩን እንዲቋቋሙና ከብክለት የፀዳ አረንጓዴ የኃይል አቅርቦት እንዲኖራቸው ለማድረግ የገባውን ቃል እያሟላ አይደለም፡፡ እስካሁን በየአካባቢዎቹ ለፕሮጅክቱ የሚለቀቀው  የአየር ንበረት ፈንድ ከ10 በመቶ በታች መሆኑን በግኝታቸው አመልክተዋል፡፡ይህም እየሆነ ያለው የልማት ባንኮችና የአለም አቀፍ  ድርጅቶች በየአካባቢው ለአነስተኛ ፕሮጀክቶች የሚለቀቁት በጀት በመዘግየቱ መሆኑን መቀመጫውን በለንደን ያደረገው አለም አቀፉ የአካባቢ ጥበቃና ልማት ተቋም ገልጿል፡፡

በሌላ በኩል  ፕሮጀክቶችን በአግባቡ መንደፍና  መገምገም  እንዲሁም ፕሮጀክቶችን   ለማስተግበሪያ የሚሙሉ ቅፆች ውስብስብነት ጊዜ የሚፈጁ በመሆናቸው ፈንዱ ለአነስተኛ ፕሮጀክቶች በወቅቱ እንዳይለቀቅ ሌላው ምክንያት ነበር ብሏል የጥናቱ ግኝት፡፡

የፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ጉቤኤም ቢሆን  በየአካባቢው የሚተገበሩ የአየር ንበረት ለውጥ ፈንድ ፕሮጀቶች ድጋፉን የሚያገኙበት አግባብ አለመለየቱ ሌላ ችገር ተደርጎም ተቀምጧል፡፡

በኢንዱስትሪ የበለፀጉ አገራት በአየር ንብረት ለውጥ ለተጎዱ አገራት መቋቋሚያ እንደ እ.ኤ.አ በ2020 በየአመቱ 100 ቢሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ቢገቡም ብዙም ገፍተው አለመሄዳቸው  ችግሩን እንዳባባሰው ተመልክቷል፡፡

እንደ ሮይተርስ ዘገባ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገራት በየአመቱ ለአረንጓዴ የኃይል ልማት ማግኘት የነበረባቸውን የ7.5 ቢሊዮን ዶላር በጀት ባለመግኘታቸው ፕሮጀክታቸው ላይ ተፅዕኖ ፈጥሯል፡፡

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ለዘርፉ ልማት እያገኘች ያለው ድጋፍ ታድያ ከ200 ሚሊዮን ዶላር የሚበልጥ አይደለም ብሏል የግኝት ሪፖርቱ፡፡

እናም በማደግ ላይ ያሉ አገራት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና ለአረንጓዴ  የኃይል ልማት ፕሮጀክቶች የተመደበላቸውን በጀት በወቅቱ እንዲያገኙ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ጥናቱ አመልከቷል፡፡

ምንጭ ፡‑ ሮይተርስ