ኢትዮጵያ የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንቷን በ10 እጥፍ ለማሳደግ አቅዳለች

ሰኔ 10፤2009

ኢትዮጵያ የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንቷን በአስር እጥፍ ለማሳደግ ማቀዷን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ ዶ/ር አርከበ እቁባይ ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት እንደ መንገድ፤ የባቡር ሃዲድ እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን የመሰሉ በርካታ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን እያካሄደች እንደምትገኝ ተናግረዋል፡፡

ለዚህ አላማዋ ስኬት ደግሞ በሀገሪቱ የተለያዩ ኢንደስትሪያል ፓርኮች ግንባታ ዋንኛ ግብዓት ናቸው ብለዋል፡፡

ከዚህም ውስጥ የሃዋሳ ኢንደስትሪያ ፓርክ ማስፋፊያ ግንባታ ተጠናቆ በመጪው ማክሰኞ የሚመረቅ ሲሆን ከ60 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይግመታል፡፡

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2016 ከቀጥታ የውጪ ኢንቨስትመንት 3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር እንዳገኘች ተነግሯል፡፡

የተመድ የንግድና ልማት ኮንፈረንስ ባወጣው ጥናት መሰረት ኢትዮጵያ ከጨርቃጨርቅና ታያያዥ ምርቶች ከፍተኛ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በማግኘት ከቪየትናም ቀጥላ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

ምንጭ፡ ሺንዋ

በለንደን ህንጻ ቃጠሎ 8 ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አልተገኙም

ሰኔ 10፤2009