በሃዋሳ ኢንደስትሪያል ፓርክ 13 ፋብሪካዎች ስራ ጀምረዋል

ሰኔ 10፤2009

በሃዋሳ ኢንደስትሪያል ፓርክ ከሚገኙ 37 ፋብሪካዎች ውስጥ 13ቱ ስራ መጀመራቸው ተገለጸ፡፡

በኢንደስትሪ ፓርኩ የመጀመሪያ የግንባታ ክፍል የተካተቱት ውስጥ 15 ፋብሪካዎች ግንባታ ተጠናቋል ነው የተባለው፡፡

ፓርኩ እስከ 100 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል የመፍጠር አቅም አለው ተብሏል፡፡

መንግስት ዘርፉን ለማሳደግ ባለው ጽኑ ፍላጎት፤ የሚሰጠው ድጋፍ እንዲሁም በርካታ የሰው ሃይል መኖሩ በሀገሪቱ ውስጥ በኢንቨስትመንት ዘርፉ እንድንሰማራ አድርጎናል ብለዋል በፓርኩ ስራ የጀመሩት የውጪ ባለሃብቶ፡፡

ስራ ከጀመሩት 13 ፋብሪካዎች ውስጥ ስድስቱ ደግሞ ምርታቸውን ለውጪ ሃገር ገበያ ማቅረብ መጀመራቸው ተነግሯል፡፡