በፍልስጤማዊያን የስደተኞች መጠለያ 65 ጥንድ ተጋቢዎች በአንድነት ተሞሸሩ

ነሐሴ 05፣2009

በፍልስጤማዊያን የስደተኞች መጠለያ 65 ጥንድ  ተጋቢዎች በአንድነት ተሞሸሩ፡፡

በፍልስጤም ምዕራባዊ ዳርቻ አልፈራ በተባለው የስደተኞች መጠለያ ካምፕ የነበሩ ፍልስጤዊያን ናቸው በአንድነት የተሞሸሩት፡፡

የ65ቱን ጥንድ ሙሽሮች ሙሉ ወጪ የፍልስጤ ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ ሸፍነውታል ተብሏል፡፡

የጥንዶቹ ሰርግ ፍልስጤማዊያን ምንም እንኳን በሰቆቃ ውስጥ አየኖሩ ቢሆንም ብሩህ ተስፋ መኖሩን ለማሳየት ነው ተብሏል፡፡

ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስን ጨምሮ በርካታ ፍልስጤማዊያን የጥንዶቹን ሰርግ ታድመዋል፡፡

በአቅም እጦት ማግባት ሳይችል ለረጅም ጊዜ የቆየው የ46 ዓመቱ አህመድ አል አርጃ ሰርጉ ዳግም የተፈጠርኩ ያህል እንዲሰማኝ አድርጓል ብሏል፡፡

ለ65ቱ ጥንዶች ሰርግ 2መቶ ሺህ ዶላር ወጪ ተደርጓል፡፡

ምንጭ፡‑ ሽንዋ