በግብጽ በደረሰ የባቡር አደጋ 41 ሰዎች ሞቱ

ነሀሴ 6 ፤2009

በግብጽ የባህር ዳርቻ አሌክሳንዴሪያ ከተማ ሁለት የመንገደኞች ባቡር በመጋጨታቸው 41 ሰዎች ሲሞቱ ከ120 በላይ የሚሆኑት ደግሞ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለጸ፡፡

የሀገሪቱ የትራንስፖርት ሚኒስትር ሂሻም አራፋት አደጋው የተፈጠረው ትክክለኛው ጥንቃቄ ባለመወሰዱ በሰራተኞች የተፈጠረ አደጋ ነው ብለዋል፡፡

የግብጽ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታ አልሲሲ የአደጋው መንስኤ እንዲጣራ የወሰኑ ሲሆን ለተጎጂ በተሰቦችም መንግስት አስፈላጊውን ካሳ እንደሚከፍል ቃል ገብተዋል፡፡

ሌሎች የመገናኛ ብዙሃን ደግሞ የሟቾቹ ቁጥር እስከ ሃምሳ ሊደርስ እንደሚችል እየዘደቡ ይገኛሉ፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ