ውሽንፍር ዝናብ የቀላቀለው ሀሪኬን ኢርማ የተባው አውሎ ነፋስ በካሪቢያን ደሴቶች ላይ 95 በመቶ ውድመት አስከትሏል

ጳጉሜ 02፣2009

ውሽንፍር ዝናብ የቀላቀለው ሀሪኬን ኢርማ የተባው አውሎ ነፋስ በካረቢያን ደሴቶች ላይ 95 በመቶ ውድመት አስከትሏል፡፡

ሃሪኬን ኢርማ በመባል የሚጠራው ዝናብ የቀላቀለው ከባድ አውሎ ነፋስ በአሜሪካ ግዛቶች በመለስ ሲያደርስ የነበረው ጉዳት ወደ ካረቢያን አካባቢ ተሸጋግሯል፡፡

አውሎ ነፋሱ በአንቲጓና ባርቡዳ ደሴቶች ላይ ከፍተኛውን ጉዳት አድርሷል ተብሏል፡፡

ባርቡዳ የተባለችው ትንሿ ደሴት ብቻ ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎች እንደሞቱ ነው ተገልጿል᎓᎓

95 በመቶ የሚሆነው የአገሪቱ ክፍል ውድመት እንደደረሰ የአንቲጓና ባርቡዳ ጠቅላይ ሚንስትር ጋስቶን ብራውን ተናግረዋል፡፡

ጉዳቱ ከፍተኛ ስለሆነ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ተብሏል᎓᎓

ከደሴቷ ነዋሪዎች መካከል ግማሽ የሚሆኑት 3 ሚሊዮን ነዋሪዎች በሃሪኬን ጉዳት ምክንያት የኤሌክትሪክ ሃይል ተቋርጦባቸዋል ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ᎓᎓

ሃላፊዎቹ እንደሚሉት የኤሌክትሪክ ሃይል መቋረጡ ለብዙ ቀናት ሊቀጥል ይችላል ተብለዋል᎓᎓

ደሴቶቹ ከደረሰባቸው አደጋ ለማገገም 100 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግም ተገልጿል፡፡    

ከሀሪኬን ኢርማ አውሎ ነፋስ በተጨማሪ ሁለት ሌሎች ሃይለኛ ማእበሎች ወደ ሃሪኬንነት በሌሎች የካሪቢያን አካባቢ ይቀየራሉ ተብሎም ስጋት ተፈጥሯል᎓᎓

ኢርማ ከአምስት ሃሪኬኖች አንዱ የሆነውና ዝናብ አዘል ከፍተኛ አውሎ ነፋስ ዓይነት ነው፡፡

ምንጭ፡‑ ቢቢሲ