ሞዛምቢክ በከፈተችው የፀረ ሙስና ዘመቻ 28 ባስልጣናትን ለፍርድ አቀረበች

መስከረም 03፣2010

ሞዛምቢክ በከፈተችው የፀረ ሙስና ዘመቻ 28 ባስልጣናትን ፍርድ ቤት አቀረበች፡፡

የአገሪቱ የፀረ ሙስና ባለስልጣናት ከብሄራዊ የግብርና ፈንድ 2.7 ሚሊዮን ዶላር መዝብረዋል በሚል ተጠርጥረው ነው ለፍርድ የቀረቡት፡፡

የፈንዱ የቀድሞ ኃላፊዋን ጨምሮ 28ቱ ተከሳሾች ያልተተገበረን ፕሮጀክት በሃሰት  ሪፖርት በማድረግ በማጭበርበር፣በሙስና፣ስልጣንን ተገን በማድረግ በመጠቀም፣ያልተገባ ጥቅም እንዲከፈል በማድረግና ሌሎች ጉዳዮችን ጨምሮ 355 የክስ ዓይነቶች ይጠብቃቸዋል፡፡

የአገሪቱ አቃቤ ህግ ተከሳሾቹ ላይ የተደራጀ ማስረጃ ማግኘቱን አመልክቷል፡፡

ሞዛምቢክ ብሄራዊ የግብርና ፈንድ ብላ ያቋቋመችው መስሪያ ቤት የግብርናውን ዘርፍ ምርታማነት ለመሻሻል በማለም ነበር፡፡

ከሁላት ወራት በፊት ሞዛምቢክ የፍትህ ሚንስትሯን የአገር ሀብት ያለአግባብ በመመዝበር ወንጅላ የሁለት ዓመት እስር እንዲፈረድባቸው ማድረጓም ይታወቃል፡፡

ምንጭ፡‑ ሽንዋ