አፍሪካ በየአመቱ 60 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደምታጣ አንድ ሪፖርት ይፋ አደረገ

መስከረም 26፣2010

አፍሪካ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር በተለይም በህገ ወጥ የማዕድናት ዝውውር በአመት ወደ 60 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደምታጣ አንድ ሪፖርት አመልክቷል᎓᎓

ክፍተቱን ለመሙላትም አዳዲስ የስትራቴጂክ ፖሊሲዎችን መተግበር እንደሚገባ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ ዶክተር ቬኔሳ ኡሼ ተናግረዋል፡፡

አፍሪካ ያላትን የተፈጥሮ ሃብት ተጠቃሚ መሆን ያለመቻሏን የገለጹት ዶክተር ቬኔሳ ኡሼ በህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር በተለይም  በማዕድን ዘርፉ የሚታየው ህገ ወጥ ግብይት ዋናው ምክንያት መሆኑን ጠቁመዋል᎓᎓

አፍሪካ ያላት ማአድን በድብቅ ስለሚወጣ አህጉሪቱ ከቀረጥ ማግኘት የሚገባትን ገቢ እንዳታገኝ አድርጓታል ብለዋል ᎓᎓

ምንጭ፤ ኒውስ 24