የኬንያ አጠቃላይ ምርጫ የፊታችን ጥቅምት 16 ድጋሚ ሊካሄድ ነው

መስከረም 29፣2010

የኬንያ አጠቃላይ ምርጫ የፊታችን ጥቅምት 16 ዓ.ም ድጋሚ እንደሚካሄድ የሀገሪቱ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

ቦርዱ ይህን የተናገረው የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለፈው ሐምሌ ወር የተካሄደውን አጠቃላይ ምርጫ የሰረዘበትን ምክንያት በዝርዝር ካስታወቀ በሃላ ነው ተብሏል፡፡

በወቅቱም የሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች ውጤት ሳይቆጠር ፕሬዝዳንት አሁሩ ኬንያታ ምርጫውን እንዳሸነፉ መነገሩ ለምርጫው መሰረዝ አንዱ ምክንያት እንደሆነ ፍርድ ቤቱ መግለፁ ይታወሳል፡፡

በዚህና በሌሎች ምክንያቶች ፍርድ ቤቱ የሀገሪቱን ምርጫ ቦርድ ወቅሶ ነበር፡፡

ምርጫው ጥቅምት 7 እንዲካሄድ ቢወሰንም ለምርጫው ማስኬጃ የሚውሉ የኮምፒውተር ማሻሻያ ስራዎች በጊዜ መጠናቀቀ ስለማይችሉ ምርጫው ለጥቅምት 16 መሸጋገሩን ተነግሯል፡፡

የመጀመሪያው ምርጫ በህገ መንግስቱ መሰረት አለመካሄዱን አረጋግጦ የምርጫው ውጤቱን የሰረዘው ፍርድ ቤቱ፤ በ60 ቀናት ዳግም አጠቃላይ ምርጫው እንዲካሄድ ማዘዙን አይዘነጋም፡፡ 

ምንጭ፦ቻይናዴይሊ እና ጋርዲያን ድረ-ገጾች