በኤጀርሳ ላፍቶ ወረዳ ከአንድ ሄክታር መሬት እስከ 45 ኩንታል ምርት ይጠበቃል

ጥቅምት 8 ፤2010

የተሻሻሉ የስንዴ እና ጤፍ ዝርያዎችን በመጠቀማቸው የተሻለ ምርት እንደሚጠብቁ በምዕራብ ሸዋ ዞን የኤጀርሳ ላፍቶ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለፁ፡፡

በነዚህ በተሻሻሉ ዝርያዎች ከአንድ ሄክታር መሬት እስከ 45 ኩንታል ምርት እንደሚጠብቁም ነው አርሶ አደሮቹ ያስታወቁት፡፡