ሶማሊያ 81 የአልሸባብ ታጣቂዎች መግደሏን አስታወቀች

ህዳር 3፣2010

የሶማሊያ የደህንነት ሃይል ጂሊብ በተባለች አውራጃ የአልሸባብ  ካምፕን በማጥቃት 81 ታጣቂዎች መግደሉን አስታውቋል።

የሀገሪቱ የማስታወቂያ  ሚንስትር አብዱራህማን ኡስማን እንደገለጹት ታጣቂዎቹ የተገደሉት የሶማሊያ ጦርና አጋሮቹ ባካሄዱት ዘመቻ ነው።

በጥቃቱ የታጣቂዎቹ ተሽከርካሪዎችና   ከባድ የጦር መሳሪያዎችም ተደምስሰዋል ተብሏል።

በተመሳሳይ አሜሪካ ሼቤል በተባለች የሶማሊያ ግዛት በሰው አልባ አውሮፕላን በፈጸመችው ጥቃት በርካታ የአልሸባብ ታጣቂዎች መገደላቸውን በአፍሪካ የአሜሪካ ዕዝ ገልጿል።

ጥቃቱ ከሶማሊያ መንግስት ጋር በመቀናጀት የተፈፀመ መሆኑንም አሜሪካ አስታውቃለች፡፡

የትራምፕ አስተዳደር ቀደም ብሎ በምስራቅ አፍሪካ ያለውን ሽብርተኝነት ለመከላከል ወታደራዊ እንቅስቃሴውን እንደሚያጠናክር መግለጹን የአሶሼትድ ፕረስ በዘገባው አስታውሷል፡፡