ሶማሊያ በድርቁ ምክንያት ከ100 በላይ ሰዎች እንደሞቱባት አስታወቀች

የካቲት 27፣2009

ሶማሊያ በድርቁ ምክንያት በአንድ ቀጠና ብቻ ከ100 በላይ ሰዎች እንደሞቱባት አስታወቀች፡፡

የሶማሊያው ጠቅላይ ሚንስተር  ሀሰን ዓሊ እንደተናገሩት ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ  ድርቁ በከፋት አካባቢ በርሃ 110 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

በደቡባዊ ሶማያሊያ ድርቁ በሰው ህይወት ላይ ያስከተለውን ጉዳት ሶማሊያ በይፋ ስትግልፅ ይህ የመጀመሪያዋ ነው፡፡

ድርቁ እያደረሰ ያለው ጉዳት በሶማሊያ ከቁጥጥር ውጭ እንዳይሆን በእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ዘንድ  ስጋት ደቅኗል፡፡

እንደ ቢቢሲ ዘገባ በአሁኑ ጊዜ ሶስት ሚሊዮን የሚሆኑ ሶማሊያዊያን ለምግብ ዋስትና ችግር ተጋልጠዋል፡፡

በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተው ድርቅ ደቡብ ሱዳንን፣ኬንያንና  በኢትዮጵያ አርብቶ አደር አካባቢዎች ድጋፍ እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግሰታት ድርጅት የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ፕሮግራም ክፍል ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡