የቻይናው ኩባንያ በኢትዮጵያ ለ100ሺህ ዜጎች ስራ ሊፈጥር ነው

የካቲት 30፣ 2009

የጫማ ምርቶችን ለገበያ የሚያቀርበው የቻይናው ዣንግ የጫማ ፋብሪካ ለ100 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ማቀዱን አስታውቀ፡፡

ዣንግ ይህን ያለው ኢትዮጵያ የመሰል ምርቶች  ማዕክል ለመሆን ያቀደችውን ለማሳካት ነው፡፡

በቀጣይ የማስፋፊያ ግንባታ በመስራት አሁን በስራ ላይ የሚገኙትን 6 ሺህ ሰራተኞች ወደ 100ሺህ አሳድጋለሁ ብሏል፡፡

የኩባንያው ምርቶች በምዕራባውያን ተቀባይነትን በማግኘቱ በውጭ ምንዛሪ የአገሪቱን ኢኮኖሚ መደገፉንም ገልጿል፡፡

ኩባንያው የሀብት መጠኑንም 10 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ማቀዱን አስታውቋል፡፡

ምንጭ፡-ኢ ኤን.ፒፕል