የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በሃምሌ ወር 1.1 ቢሊየን ብር ዋጋ ያለው ምርት ማገበያየቱን አስታወቀ

ነሐሴ 05፣2009

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለፈው ሃምሌ ወር 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ዋጋ ያለው ምርት ማገበያየቱን አስታወቀ፡፡

ቡና ሰሊጥ እና ነጭ ቦሎቄ የተገበያዩ ምርቶች ናቸው፡፡

ከተገበያዩት ምርቶች ውስጥ ቡና በመጠን 49 በመቶ በምርት ዋጋ 7 በመቶ በመያዝ ቀዳሚ ነው፡፡

ከሰኔ ወር ጋር ሲነፃፀርም የቡና ዋጋ 1 ነጥብ 3 በመቶ፣ የሰሊጥ ደግሞ 13 በመቶ ጭማሪ አሣይቷል ብሏል ምርት ገበያው፡፡

ለውጪ ገበያ በሚቀርቡ ምርቶች ቡና በመጠንም ሆነ በግብይት ዋጋ ከግማሽ በላይ ድርሻን ይዟል፡፡ መረጃውን ያደረሰን የምርት ገበያው ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ነው፡፡