ብሩንዲ 1ሺህ 8 መቶ በላይ ሰላም አስከባሪ ወደ ሶማሊያ ላከች

ነሃሴ 24፤2009

ብሩንዲ በአሚሶም ስር የሚገኘውን የሶማሊያ ጦር የሚያግዝ 1ሺህ 8 መቶ 19 የጦር ሰራዊት አባላትን ወደ ሶማሊያ ላከች፡፡

በሶማሊያ ለተሰማራው የአሚሶም ጦር ብሩንዲብዙ ጦር ያዋጣች ሀገር ነች፡፡

እ.አ.አ ከ2007 ጀምሮ ብሩንዲ ከ5 ሺህ በላይ ወታደሮችን በሶማሊያ ማሰመራት ችላል፡፡

ብሩንዲ አሁን የላከችው ጦር በስፋራው የነበረውን የሀገሪቱን ጦር የሚተካ ነው ተብሏል፡፡

በአልሸባብ የሽብር ተግባር የምትታመሰው ሶማሊያ የኢትዮጵያን ጦር ጨምሮ በኬኒያ እና በሌሎች ሀገራት የሰላም አስከባሪ ጦር ድጋፍ ሰላም ለማግኘት እየሰራች ነው፡፡

ዘገባው የዥንዋ ነው፡፡