በበጀት አመቱ ከ1.7 ሚሊዮን በላይ የስራ እድል መፈጠሩን ሚኒስቴሩ አስታወቀ

ነሃሴ 29፤2009

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በከተሞች ከ1 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ የሥራ ዕድል መፈጠሩን የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በከተሞች የሚታየውን የመኖሪያ ቤት ዕጥረት ችግር ለመፍታትም የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት ተጨማሪ አማራጭ ሆነው እንደሚቀጥሉ ተጠቁሟል፡፡

14ኛው የከተማ ልማትና ቤቶች ዘርፍ ጉባኤ በጋምቤላ እየተካሄደ ነው፡፡