በአሜሪካ የአየር ጥቃት 100 የአልሸባብ ታጣቂዎች ተገደሉ

ህዳር 13 ፣2010

አሜሪካ በሶማሊያ በፈጸመችው የአየር ጥቃት 100 የአልሸባብ ታጣቂዎች ተገደሉ።

በሰው አልባ አውሮፕላን በተፈጸመው የአየር ጥቃት አንድ መቶ ታጣቂዎች መገደላቸውን የአሜሪካ መከላከያ ሀይል ገልጿል።

ጥቃቱ የተፈጸመው ከዋና ከተማዋ ሞቃድሾ ሰሜና ምዕራብ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት በሚገኘው በአልሸባብ ማስልጠኛ ካምፕ መሆኑንም ተመልክቷል።

አሜሪካ በተያዘው የአውሮፓውያኑ አመት በሶማሊያ የሚንቀሳቀሱ በርካታ አሸባሪዎች መግደሏ ዘገባው አስታውሷል።