የአውሮፓ ህብረት ለምስራቅ አፍሪካ ተረጅዎች 165 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ሊሰጥ ነው

መጋቢት  11፣2009

የአውሮፓ ህብረት በምስራቅ አፍሪካ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ለተራቡ ዜጎች ድጋፍ የሚደርስ 165 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የአሁኑ ድጋፍ ህብረቱ ከዚህ ቀደም ቃል ከገባው ውጭ የተሰጠ መሆኑ ታውቋል፡፡

በድጋፉ የሶማሊያ እና የደቡብ ሱዳን ዜጎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡

ህብረቱ ከሚሰጠው ድጋፍ 1መቶ ሚሊዮን ዩሮ የሚሆነውን በደቡብ ሱዳን ለተከሰተው ቀውስና ከአገሪቱ ወደ ጎረቤት አገራት ለተሰደዱ ስደተኞች  ጊዜያዊ መፍትሔ የሚውል ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በሶማሊያ፣ ኬኒያ እና ኢትዮጵያ ለተከሰተው የድርቅ አደጋ 65 ሚሊዮን ዩሮ መመደቡን ዘገባው ገልጿል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ባለፈው ዓመት ለቀጠናው  ድጋፍ የሚውል አራት መቶ ሚሊዮን ዩሮ መድቦ እንደነበርም ብሉምበርግ በዘገባው አስታውሷል፡፡