ጃፓን በጋምቤላ ክልል ለሚገኙ ስድተኞች የ2.4 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ሰጠች

ጥቅምት 10፤2010

ጃፓን በጋምቤላ ክልል ለሚገኙ ስደተኞች የትምህርት ቤት ግንባታ የሚውል የ2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገች፡፡

ድጋፉ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በካምፖቹ ለመገንባት የሚያስችል ሲሆን ስደተኞች ከስደተኛ ተቀባይ ህዝብ ጋር ተላምደውና ተባብረው እንዲኖሩ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የትምህርት ቤቶቹ መገንባት ከ5ዐሺ በላይ የአካባቢዎችን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡

የጃፓን ኤምባሲ ኢኮኖሚክ ኦፊሰር ዮሒ ኦቶሞ ፕሮጀክቱ ሁሉም ሰው በማንኛውም ሁኔታ የመማር መብቱን እንዲጠቀም ያግዛል ብለዋል፡፡

ጃፓን እስከአሁን በጋምቤላ ክልል ለሚገኙ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ከ2ዐ ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ አድርጋለች፡፡