አሜሪካ ዛሬ የ2 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ ሙሉ የፀሀይ ግርዶሽን ታስተናግዳለች

ነሐሴ 15፣2009

አሜሪካ ዛሬ የ2 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ ሙሉ የፀሀይ ግርዶሽን ታስተናግዳለች፡፡

በርካታ አሜሪካዊያን ታዲያ ከ240 ዓመት የአገራቸው ውልደት በኃላ የሚከሰተውን ይህን ሙሉ የፀሀይ ግርዶሽ ለማየት በጉጉት እየተጠባበቁ ነው፡፡

የሙሉ የፀሀይ ግርዶሽ በአሜሪካ የሚከሰተው ሙሉ ጨረቃ ከምዕራባዊ አሜሪካ ኦሪጎን ወደ ደቡባዊ ካሮሊና ግዛት አቅጣጫ ፀሀይን በትይዩ  ሸፍናት ስታልፍ ነው ፡፡

በአሜሪካ ታሪክ የፀሀይ ግርዶሹ አትላንቲክና የሰላማዊ ውቅያኖስ ዳርቻን ሲያዳርስ እ.ኤ.አ ከ1918 ወዲህ የአሁኑ የመጀመሪያው ነው ብለዋል ተመራማሪዎች፡፡

በተለይም  በአሜሪካ ምድር የሚከሰተው የዛሬውን ሙሉ የፀይ ግርዶሽ አገሪቱ ከተመሰረተች ወዲህ የመጀመረያው ያደርገዋልም ተብሏል፡፡

ዛሬ ይታያል ተብሎ የሚጠበቀውን ይህን ሙሉ የፀሀይ ግርዶሽ ለመከታተል በርካቶች በጉጉት እየተጠባበቁ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ይሁን እንጂ 2 ደቂቃ ከ40 ሰኮንድ የሚቆየውን ሙሉ የፀሀይ ግርዶሽ ትዕይንት ለመታደም የጠራ ሰማይ መኖር ወሳኝ ነው ተብሏል፡፡

ታዳሚዎች ያለ መመልከቻ መነፅር ሙሉ የፀሀይ ግርዶሹን እንዳይመለከቱ ተመክሯል፡፡

ከአሜሪካ ውጭ የደቡብ አሜሪካ ሰሜናዊ አገራትና የሰሜን አሜሪካ አገራት ከፊል የፀሀይ ግርዶሹን ሊያዩ ይችላሉ ተብሏል፡፡

ሙሉ የፀይ ግርዶሽ የሚከሰተው ጨረቃ ፀሐይን በትዩዩ ሸፍና ስታልፍ የሚከሰተው ትዕይንት ነው፡፡

ምንጭ፡‑ ቢቢሲ