ኢትዮጵያ በ2ዐዐ9 ከ3ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ስባለች

ህዳር 1፤2010

ኢትዮጵያ ባለፈው 2ዐዐ9 ዓ.ም ከ3ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን መሳብ ችላለች፡፡

በተያዘው ዓመትም አራት ቢሊዮን ዶላር የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ለመሳብ መታቀዱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በዚህ ዓመት አንደኛ ሩብ አመትም 5ዐዐ ሚሊየን ዶላር ማሳካት መቻሉን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገልጿል።