የ2010 የከፍተኛ የትምህርት ተቋም መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ

ነሐሴ 25፣2009

የ2010 የከፍተኛ የትምህርት ተቋም መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ፡፡

አገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አጄንሲ ዛሬ በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በዘንድሮው አመት የመሰናዶ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው ወደ ለ2010 የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን መግቢያ ነጥብ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚሁ መሰረት  በተፈጥሮ ሳይንስ መስክ

ለመደበኛና ማታ ተፈታኞች

 • ለወንዶች የመግቢያ ነጥብ 352 እና ከዚያ በላይ
 • ለሴቶች 330 እና ከዚያ በላይ

ለታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢዎች 

 • ለወንዶች 320 እና ከዚያ በላይ
 • ለሴቶች 305 እና ከዚያ በላይ

መስማት ለተሳናቸው ተፈታኞች

 • ለሁለቱም ጾታ ተፈታኞች 275 እና ከዚያ በላይ

ለግል ተፈታኞች

 • ለወንዶች 360 እና ከዚያ በላይ
 • ለሴቶች 355 እና ከዚያ በላይ እንዲሆን ተቆርጧል፡፡

ኤጀንሲው ለማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የከፍተኛ ትምህርት ነጥብ መግቢያንም ይፋ አድርጓል፡፡

ለመደበኛ ለማታ ተማሪዎች

 • ለወንድ 335 እና ከዚያ በላይ
 • ለሴት 320 እና ከዚያ በላይ

ድጋፍ ለሚሹ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢ ተፈታኞች ደግሞ

 • ለወንድ 315 እና ከዚያ በላይ
 • ለሴት 300 እና ከዚያ በላይ

መስማት ለተሳናቸው ተፈታኞች

 • ለሁሉም ጾታዎች 275 እና ከዚያ በላይ

ለግል ተፈታኞች ደግሞ

 • ለወንዶች 360 እና ከዚያ በላይ
 • ለሴቶች 355 እንዲሆን መቆረጡን አጄንሲው አመልክቷል፡፡

ሪፖርተር ፡‑ አዝመራው ሞሴ