ሳኡዲ በሙስና ምክንያት ያሰረቻቸው ሰዎች ቁጥር ከ200 በላይ ደረሰ

ህዳር 1፤2010

ሳውዲ አረቢያ በሙስና ምክንያት ጠርጥራ ያሰረቻቸው ልኡላንና የአገሪቱ ባለሀብቶች ቁጥር ከ200 በላይ መድረሱን አስታውቃለች፡፡

ባለፈው ሳምንት ዘመቻ በሚመስል መልኩ በተጀመረው እስር 11 ልኡላንና ንጉሳዊያን ቤተሰቦችና ባለሃብቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የሳውዲ ጠቅላይ አቃቢ ህግ የሆኑት ሼክ ሳውድ አልሞጀብ ሀሙስ እለት በሰጡት መግለጫ በታሳሪዎቹ ላይ የሚደረገው ምርመራ እየተፋጠነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አገሪቱ በስልት በተሰራ ሙስና እና ማጭበርበር ምክንያት ከ100 ቢሊዮን ዶላር በላይ ማጣቷንም ነው ጠቅላይ አቃቢ ህጉ ያስታወቁት፡፡

ምንጭ፡- ዋሽንግተን ፖስት