ኢትዮ ቴሌኮም በ2017 በ57 ሚሊዮን ደንበኞቹ ከአፍሪካ ቀዳሚው የቴሌኮም ኩባንያ ሆነ

ህዳር8 ፤2010

ኢትዮ ቴሌኮም በሞባይል ደንበኞች ቁጥር  በ57 ሚሊዮን ደንበኞቹ  ከአፍሪካ ግዙፉ የቴሌኮም ደረጃን ከናይጀሪያው ኤም ቲኤን ኩባንያ ተቀብሏል፡፡

አይ.ቲ ዌብ የተባለው ድርገፅ እንደዘገበው  ኢትዮ ቴሌኮም እ.ኤ.አ በ2017 ዓ.ም መጨረሻ ላይ የሞባይል ደንበኞቹን ብዛት ከ57 ሚሊዮን በላይ በማድረሱ ከአፍሪካ ቁጥር አንድ ግዙፍ ኩባንያ መሆን የቻለው፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በሞባይል ደንበኞች ብዛት ከአፍሪካ ግዙፍ ኩባንያ የነበረውን  የናይጀሪያውን ኤም.ቲ.ኤን. የቴሌኮም ኩባንያ በመቅደም ጭምር ቀዳሚነቱን አረጋግጧል ብሏል ዘገባው፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ሶስት አመታት  በ1.6 ቢሊዮን ዶላር ባሄደው ማስፋፊያ

ከ62 ሚሊዮን በላይ የሞባይል ኔትወርክ፣ ከ21 ሺህ ከ.ሜ. በላይ የኦፕቲካል ፋይበር መስመር፤ ከ3 ሚሊዮን በላይ የመደበኛ መስመር መፍጠሩ ተመልክቷል፡፡

በመሆኑም የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ መጠናቀቅ ኢትዮ ቴሌኮምን ለዚህ ስኬት እንዳበቃውና ከአፍሪካ ግዙፉ ኩባንያ እንዲሆን እንዳስቻለው ኢትዮ ቴሌኮም ገልጿል፡፡