ብሪታንያ በ2040 በናፍጣና በቤንዚን የሚሰሩ መኪኖችን ሽያጭ ልትከለክል ነው

ሐምሌ 19፣2009

ብሪታንያ በ2040 በናፍጣና በቤንዚን የሚሰሩ መኪኖችን ሽያጭ ልትከለክል ነው፡፡

ብሪታንያ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ሽያጭ በህግ ለመከልከል ያሰበችው የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ በማሰብ  ነው ተብሏል፡፡

የአገሪቱ መንግስትም ይህን እርምጃ ይፋ ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢንዲፔንዴንት ዘግቧል፡፡

እስከዚያው ድረስ ግን በናፍጣና በቤንዚን የሚሰሩ መኪኖች የሚያደርሱትን የአየር ብክለት ለመቆጣጠር 255 ሚሊዮን ፓውንድ በጀት መመደቡም ተመልክቷል፡፡

እ.ኤ.አ በ2040 ይወሰዳል የተባለው እርምጃ ግን የዘገየ በሚል ተችዎች አጣጥለውታል፡፡የአገሪቱ ሊበራል ዲሞክራሲ አራማጆች እቅዱ ተግባር ላይ መዋል ካለበት በ2025 መጀመር እንዳለበት አመልክተዋል፡፡

ኢንድፔንዴንት እንደዘገበው በብሪታኒያ በየዓመቱ በአየር ብክለት ብቻ 40ሺ ዜጎቿን ታጣለች፡፡