አሜሪካና ቻይና የ250 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ስምምነት ተፈራረሙ

ጥቅምት 30 ፤2010

አሜሪካና ቻይና በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ የ250 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት መፈራረማቸው ተገለጸ፡፡

ከእነዚህ የንግድ ስምምነቶች መካከልም ቦይንግ፤ ጄኔራል ኤሌክትሪክና ኳልኮም ከአሜሪካ ተቋማት እንዲሁም የቻይና አቪዬሽን፤ የቻይና የተፈጥሮ ጋዝና ነዳጅ አምራች ኩባኒያዎች የተካተቱበት ተጠቃሽ ነው፡፡

የቻይናው የንግድ ሚኒስትሩ ዚሆንግ ሻን የተደረገው የንግድ ስምምነት እጅጉን አመርቂ ሲሉ አወድሰውታል፡፡

በቻይና የአሜሪካ የንግድ ምክር ቤት ሊቀመንበር ዊሊያም ዛርት በበኩላቸው የተደረገው የንግድ ስምምነት በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለው የኢኮኖሚ ግንኙነት እየጠነከረ መምጣቱን ያሳያል ብለዋል፡፡

ሁለቱ ሃገራት ይህንን ስምምነት ይፈጽሙ እንጂ አሁንም ቻይና ላይ ቅራኔ ፍትሃዊ የንግድ ምጣኔን ማስፈን አልቻለችም በማለት አሜሪካ ክስ ታቀርባለች፡፡

ይህ የንግድ ስምምነት በቻይና ጉብኝት እያደረጉ ላሉት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንደ አንድ ትልቅ ውጤት ሆኖ ሊቀጠርላቸው ይችላል እየተባለ ነው፡፡

ዋንኞቹ የንግድ ስምምነቶች

ከተደረጉት የንግድ ስምምነቶች መካከል በዋነኛነት የሚጠቀሱት የቻይናው ኢነርጂ ኢንቨስትመንት በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ውስጥ ለ20 አመታት የተፈጥሮ ጋዝና ኬሚካሎችን ለማምረት የ83.7 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ፈጽሟል፡፡

ኳሊኮም በበኪሉ ዣኦሚ፤ ኦፒፒኦና ቪቮ ከተባሉት አነስተኛ የኤሌክትሮኒክ እቃዎች አምራች ጋር የ12 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ፈጽሟል፡፡

ቦይንግ ደግሞ 300 አውሮፕላኖችን በ37 ቢሊዮን ዶላር ለቻይና አየር መንገዶች ለመሸጥ ቃል ገብቷል፡፡

ምንጭ፡ ሮይተርስ