በኢራቅ እና ኢራን በተከሰተ ርዕደ መሬት ከ335 በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ 4 ሺህ ደግሞ ቆስለዋል

ህዳር 04 ፣ 2010

በኢራቅ እና ኢራን አዋሳኝ ድንበር 7.3 ሬትክተር ስኬል በተመዘገበ ርዕደ መሬት  ከ335 በላይ ሰዎች ሲሞቱ ፣ 4 ሺህ ገደማ የሚሆኑት መቁሰላቸው ተዘግቧል፡፡

አንድ የኢራንን ረድኤት ድርጅት ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው በአደጋው ሳቢያ 70 ሺህ ሰዎች ጊዚያዊ መጠለያ ያስፈልጋቸዋል፡፡

በደረሰው አደጋ አብኛዎቹ ሟቾች  የምእራብ ኢራን ኬርማንሻህ  ግዛት ነዋሪዎች ሲሆን  ሰባቱ ኢራቃዊያን መሆናቸውን ተገልጿል፡፡

የሟቾች ቁጥር  ሊጨምር እንደችልም  ተሰግቷል፡፡

ምንጭ፡‑ ቢቢሲ