በኮማንድ ፖስቱ በቁጥጥር ስር የነበሩ 9 ሺህ 800 የተሃድሶ ሰልጣኞች ተለቀቁ

ታህሳስ  12፣2009

በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ሁከት ውስጥ ተሳትፈው በማሰልጠኛ ጣቢያዎች ውስጥ የተሃድሶ ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ 9 ሺህ 800 ተጠርጣሪዎች ወደ የመጡበት መመለሳቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ገለጸ፡፡

ዛሬ የወጡት የተሃደሶ ሰልጣኞች ለ1 ወር ከ1ዐ ቀን የቆዩ መሆናቸውንና በህገ መንግስቱ፣ ሀሳብን በሰላማዊ መንገድ ስለ መግለፅ  እንዲሁም በሀገሪቱ ስላለው የስራ ዕድል ዙሪያ የግንዛቤ ስልጣና እንደተሰጣቸው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮ  ጽ/ቤት ሚንሰትር ዴኤታ አቶ ዛዲግ አብረሃ ገልጸዋል፡፡

በሁከት ውስጥ ተሳትፈው በተሃድሶ ውስጥ ከነበሩ ግለሰቦች ከትምህርታቸውና ከተሰማሩበት የመንግስት ስራ የተለዩትን ህጉ በሚፈቅደው መሰረት እንደሚስተናገዱም ተገልጿል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በስልጠና ማእከሉ ባገኙት ትምህርት በጥፋታቸው መፀፀታቸውን የገለጹት አቶ ዛዲግ በተሃድሶ ቆይታቸው ህገመንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት ተገቢው አያያዝ እንደተረገላቸውም  ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ግለሰቦች ወደማህበረሰቡ ሲቀላቀሉ ያገኙትን ግንዛቤ እንደሚያስተምሩ ገልፀዋል፡፡

እስካሁን ድረስ ከአዋሽ፣ ከአላጌና ከብር ሸለቆ የተሃድሶውን ስልጠና የወሰዱ ግለሰቦች ወደ የመጡበት መመለሳቸው ተገልጿል፡፡