የ40/60 ቤቶች ልማት ማህበራት በስራቸው ላይ ችግር እንዳጋጠማቸው አስታወቁ

ነሀሴ 4 ፤2009

በአዲስ አበባ በሚካሄደው የ40/60 ቤቶች ልማት መርሀግብር በስራ እድል ፈጠራ የተሰማሩ ማህበራት የመስሪያ ቦታና የሀይል አቅርቦት ችግር እያጋጠማቸው መሆኑን ተናገሩ፡፡

የከተማዋ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝም ማህበራቱ በሚያጋጥማቸው ተግዳሮቶችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱ የቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ ማህበራቱ ያጋጠማቸውን ችግር ለመፍታት እየሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ማህበራቱም የሚያመርቱዋቸውን ምርቶች በጥራት በማምረት እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል፡፡

በእያሱ ፈጠነ