ቆሼ አካባቢ በተፈጠረው አደጋ ለተጐዱ ቤተሰቦች የሚውል የ747 ሺ ብር ድጋፍ ተደረገ

መጋቢት  11፣2009

ቆሼ አካባቢ በተፈጠረው አደጋ ለተጐዱ ቤተሰቦች የሚውል የ747 ሺ ብር ድጋፍ ተደረገ፡፡

የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች ኮከስ በጋራ የ5ዐዐሺ ብር ድጋፍ ፣ የኢትዮጵያ የንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ሰራተኞች 157ሺ ብር እንዲሁም የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰራተኛ እና አመራሮች 9ዐሺ ብር በአጠቃላይ የ747 ሺ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ተቋማቱ በተፈጠረው አደጋ ሀዘናቸውን በመግለፅ ለተጐጂ ቤተሰቦች መፅናናት መመኘታቸውን የተቋማቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬቶች ባደረሱን ዘገባ አመልክተዋል፡፡