20 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል - ተመድ

ነሃሴ 04፤ 2009

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአለም አቀፍ ደረጃ 20 ሚሊዮን የሚገመቱ ህዝቦች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ገለፀ᎓᎓

የፀጥታው ምክር ቤት በየመን፤ በሶማሊያ፤ በደቡብ ሱዳን እና በሰሜናዊ ምእራብ ናይጀሪያ ለሰብአዊ እርዳታ የሚውል ተጨማሪ ገንዘብ አገራት እንዲያዋጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በአገራቱ የሚገኙ ተፋላሚ ወገኖች የሰብአዊ እርዳታው ለተጎጂዎች እንዲደርስ እንዲተባበሩም ድርጅቱ ጠይቋል፡፡

በምክር ቤቱ የተሰጠው መግለጫ እንደሚያብራራው በአገራቱ ውስጥ የተከሰተው ግጭትና አመፅ የሰብአዊ እርዳታ ለተጎጂዎች ለማድረስ እንቅፋት እየፈጠረ ነው᎓᎓

በመካከለኛና በረጅም ጊዜ እቅዶች ሊተገበሩ የነበሩትን የሰብአዊ እርዳታ ተግባሮች በማደናቀፍ በ4ቱም ሃገራት ረሃብ እንዲስፋፋ ግጭቱ አስተዋፅኦ አድርጓል ተብሏል᎓᎓

ተመድ በታህሳስ ወር እንዳስታወቀው ድርጅቱ ከተቋቋመ ጀምሮ ከፍተኛ የተባውን ከለጋሽ ሀገራት 4.9 ቢሊዮን ዶላር ለመስጠት ለመፍታት ቃል የተገባ ቢሆንም እስካሁን ግን ግማሽ ያህሉ ብቻ ገቢ መደረጉን የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋኒ ጁዳሪክ ተናግረዋል᎓᎓

ምንጭ፡ ሮይተርስ