ጨፌ ኦሮሚያ ለ2ዐ1ዐ በጀት ዓመት የ55 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በጀት አፀደቀ

ሐምሌ 10፣2009

ጨፌ ኦሮሚያ ለ2ዐ1ዐ በጀት ዓመት የ55 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በጀት በማፅደቅ ጉባኤውን አጠናቀቀ፡፡

6ተኛ መደበኛ ጉባኤውን ያካሄደው የጨፌ ኦሮሚያ በ3ተኛ ቀን ውሎው የጨፌ ኦሮሚያን የ2ዐዐ9 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የህብረት ስራ ማህበራት የመስኖ ውሃ አጠቃቀም አዋጅንም አፅድቋል፡፡

የክልሉን ስራ አሰፈፃሚ አካላት በድጋሚ የማዋቀር ሀላፊነትና ተግባር የሚወስነውን አዋጅም ተግባር ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

በዚህም የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽን ተጠሪነት ለክልሉ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ እንዲሆን አድርጓል፡፡

ጨፌው ለ2010 በጀት ዓመት ካፀደቀው የ55.8 ቢሊዮን ብር በጀት በተጨማሪም ለ2ዐዐ9 በጀት  አመት 5 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀትን በማፅደቅ ለሶስት ቀናት የቆየውን ጉባኤ አጠናቋል፡፡