ስማርት የመኪና ማቆሚያ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው

የቆሼ አደጋ ተጎጂዎችን የማጣራት ሂደት ክፍተት እንዳለበት ቅሬታ አቅራቢዎች ገለጹ

በሳዑዲ ዓረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሰላም ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ዝግጅት ማድረጉን መንግስት ገለፀ

ኢትዮጵያና ዛምቢያ ሶስት ስምምነቶች ተፈራረሙ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለአራት ወራት ተራዘመ

ኢትዮጵያና ዛምቢያ የጋራ ስምምንቶቻችውን የሚያስፈጽም ቋሚ የጋራ የትብብር ኮሚሽን መሰረቱ

ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚን ለመገንባት የምታደርገው ጥረት ከአፍሪካ ተምሳሌት እንደሚያደርጋት ተመድ ገለጸ

የህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያና ሱዳን ህዝቦች የጋራ ብልጽግና ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ሱዳን ገለጸች

የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በአደራዳሪ ጉዳይ ላይ ሳይግባቡ በቀጠሮ ተለያዩ

ምርጫ ምርጫ

Back

የ2007 ጠቅላላ የምርጫ ውጤት ይፋ ሆነ

ሰኔ 15፣ 2007

የኢትዮጵያ  ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ2007 ጠቅላላ የምርጫ ውጤት  ሰኔ 15፣ 2007 ይፋ አደረገ።

በመራጭነት ከተመዘገበው 36 ሚሊየን 851 ሺ 461 ህዝብ መካከል 34 ሚሊየን 351 ሺህ 444 ህዝብ (93 ነጥብ 2 በመቶ) ድምፁን ሰጥቷል።

ይፋ በተደረገው የምርጫ ውጤት መሰረት የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) በአምስት ክልሎች፣በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ከተሞች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ547 መቀመጫዎች 500 ወንበሮችን (82 ነጥብ 4 በመቶ ድምጽ በማግኘት) አሸንፏል።

የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እንደተናገሩት በምርጫው ዋጋ ካለው 33 ሚሊየን 201 ሺ 969 ድምፅ ውስጥ 27 ሚሊየን 347ሺ 332 ወይም 82 ነጥብ 4 በመቶ ድምጽ በማግኘት ነው ገዥው ፓርቲ  ያሸነፈው።

ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካሸነፉት እጩዎች መካከል 212 ወይም 38 ነጥብ 8 በመቶ ሴቶች ናቸው።

እንደ ሰብሳቢው ገለጻ የአፋር ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) በስምንት፣ የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶህዴፓ) በ24 ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ዴምክራሲያዊ ፓርቲ (ቤጉህዴፓ) በዘጠኝ ምርጫ ክልሎች አሸንፈዋል።

የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋህዴን) በሦስት ፣ የሐረሪ ብሄራዊ ሊግ (ሐብሊ) በአንድና የአርጎባ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (አህዴድ) በአንድ የምርጫ ክልሎች በማሸነፍ ቀሪዎቹን 46 መቀመጫዎችን ተቆጣጥረዋል።

በክልል ምክር ቤቶች፤ በትግራይ ክልል ምክር ቤት ካሉ 152 ወንበሮች ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሙሉውን አሸንፏል።

በአፋር ክልል ምክር ቤት ካሉ 96 ወንበሮች 93ቱን አፋር ብሄራዊ ዴምክራሲያዊ ፓርቲ ያሸነፈ ሲሆን፣ የአርጎባ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (አህዴድ) ቀሪዎቹን መቀመጫዎች ወስዷል።

በአማራ ክልል ካሉ 294 መቀመጫዎች ሙሉውን ብሄራ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ብአዴን) ያሸነፈ ሲሆን፣ በኦሮሚያ ክልል የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት(ኦሕዴድ)537 መቀመጫዎች ን ማሸነፉን ቦርዱ አረጋግጧል።

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ያሉ 273 ወንበሮች ክልሉን በማስተዳደር ላይ ያለው የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶህዴፓ) አሸንፏል።

በተመሳሳይ በጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ውስጥ ያሉትን 155 ወንበሮች በሙሉ የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋህአዴን) ማሸነፉን ይፋ ተደርጓል።

በቤንሻንጉል ጉምዝ  ክልል ምክር ቤት ያሉትን 99 ወንበሮች በሙሉ የቤንሻንጉል ጉምዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቤጉህዴፓ) አሸንፏል።

በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ውስጥ ከሚገኙ 348 መቀመጫዎች 345ቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ደኢህዴን) ማሸነፉን ቦርዱ በመግለጫው አመልክቷል።

በሐረሪ ክልል ምክር ቤት ውስጥ ካሉ 36 መቀመጫዎች 18 ቱን የሐረረ ብሄራዊ ሊግ(ሐብሊ) ያሸነፈ ሲሆን፣ ቀሪውን 18 መቀመጫዎች ኦህዴድ ተቆጣጥሯል።

ለክልል ምክር ቤቶች ካሸነፉት እጩዎች መካከልም 800 ወይም 40 ነጥብ 3 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን በመግለጫው ተመልክቷል።

ፕሮፌሰር መርጋ ለጋዜጠኞች  ባደረጉት ገለጻ እንደተናገሩት በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል በጊምቦ ገዋታ ምርጫ ክልል ዉጤት ተጠናቅቆ ለቦርዱ ቀርቦ ባለመጽደቁ በዛሬው እለት ይፋ አልተደረገም።

እንደሰብሳቢው ገለጻ ምርጫውን ለማስፈጸም ቦርዱ ለህዝብ ተወካዮችና ለክልል ምክር  ቤቶች ከሰጠው የድምፅ መስጫ ወረቀቶች መካከል 3 ነጥብ 3 በመቶው ብቻ ዋጋ አልባ ሆኗል።

በ2007 ጠቅላላ ምርጫ 58 የፖለቲካ ፓርቲዎች የተፎካካሩ ሲሆን 1ሺህ828 የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች ተወዳድረዋል።

ለክልል ምክር ቤቶች 3ሺህ991 ዕጩዎች መወዳደራቸውንም ከቦርዱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ፡-ኢዜአ