ስማርት የመኪና ማቆሚያ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው

የቆሼ አደጋ ተጎጂዎችን የማጣራት ሂደት ክፍተት እንዳለበት ቅሬታ አቅራቢዎች ገለጹ

በሳዑዲ ዓረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሰላም ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ዝግጅት ማድረጉን መንግስት ገለፀ

ኢትዮጵያና ዛምቢያ ሶስት ስምምነቶች ተፈራረሙ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለአራት ወራት ተራዘመ

ኢትዮጵያና ዛምቢያ የጋራ ስምምንቶቻችውን የሚያስፈጽም ቋሚ የጋራ የትብብር ኮሚሽን መሰረቱ

ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚን ለመገንባት የምታደርገው ጥረት ከአፍሪካ ተምሳሌት እንደሚያደርጋት ተመድ ገለጸ

የህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያና ሱዳን ህዝቦች የጋራ ብልጽግና ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ሱዳን ገለጸች

የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በአደራዳሪ ጉዳይ ላይ ሳይግባቡ በቀጠሮ ተለያዩ

ምርጫ ምርጫ

Back

በምርጫው ጊዜያዊ ውጤት ላይ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያሰሙት አቤቱታ መሰረት የሌለው እንደሆነ ቦርዱ አስታወቀ

የምርጫው ጊዜያዊ ውጤት ይፋ ከተደረገ በኋላ "ምርጫው ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ አልነበረም" በማለት አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚያሰሙት አቤቱታ መሰረት የሌለው መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ቦርዱ ሀሙስ ግንቦት 27 ፣2007 በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ሁሉም ፓርቲዎች የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ከመክፈቻ ቃለ-ጉባዔ ጀምሮ እስከ መተማመኛ ቅፅ ድረስ ሂደቱን ተቀብለውትና አምነውበት ፊርማቸውን አስቀምጠዋል።

በደምፅ አሰጣጥ ሂደቱም አንድም የፖለቲካ ፓርቲ ለቦርዱ ያቀረበው ቅሬታ አለመኖሩን ነው የገለጸው።

የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ቦርዱ ጊዜያዊ ውጤቱን ይፋ ካደረገ በኋላ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫውን ችግሮች የነበሩበት አስመስለው የሚያናፍሱት ወሬ ፍጹም ተቀባይነት የለውም።

"ምርጫው ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሁም አሳታፊ ሆኖ የበርካቶችን አመኔታ አትርፎ እያለ ፣ውጤቱ ከታወቀ በኋላ የሚነሱ መሰረተ ቢስ ምክንያቶች በቦርዱ በኩል ተቀባይነት የላቸውም" ብለዋል።

የምርጫውን አጠቃላይ ሂደትና ዴሞክራሲያዊነት አስመልክቶ ከሩብ ሚሊዮን በላይ የህዝብና የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢዎች ጭምር ማረጋገጫ መስጠታቸውን ለማሳያነት አንስተዋል።

በምርጫ ፉክክሩ ከተሳተፉት 58 የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥም በርካቶቹ የምርጫውን ሂደትና ጊዜያዊ ውጤቱን በፀጋ መቀበላቸው ፕሮፌሰ መርጋ ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች እውነታውን ወደ ጎን በመተው የህዝብን ውሳኔ ላለመቀበል ምክንያቶችን ማስቀመጣቸው ተገቢነት የሌለው እንደሆነ ነው የተናገሩት።

የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር አዲሱ ገብረእግዚያብሄር በበኩላቸው በመራጮችና በዕጩዎች ምዝገባ ወቅት ቀርበው ከነበሩት ቅሬታዎች ውጭ በድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ የቀረበ ቅሬታ የለም።

እንደ እርሳቸው ገለፃ በቅድመ ምርጫው ወቅት ቀርበው የነበሩት ወደ 48 የሚደርሱ ቅሬታዎችም ብዙዎቹ እልባት እንዲያገኙ ተደርጓል።

አምስተኛው አጠቃላይ ምርጫ ከየትኛውም ጊዜ በተሻለ መልኩ ሠላማዊ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ መጠናቀቁንም ገልጸዋል።

በተለያዩ ምክንያቶች ሳይካሄድ የቀረው የቦንጋ ገዋታ ምርጫም በመጪው ሰኔ 7 ቀን 2007 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑን ነው ቦርዱ በመግለጫው ያስታወቀው።

ምንጭ፡ ኢዜአ