የሳኡዲ አረቢያው ንጉስ የግንቦት ሃያ ደስታ መግለጫ ላኩ

የኦማን ንጉስ የግንቦት ሃያ ደስታ መግለጫ ላኩ

26ኛው የግንቦት 20 በዓል በመላ አገሪቱ እየተከበረ ነው

ግንቦት 20 አዲስ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስርዓት የፈጠረ መሆኑን ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ገለጹ

26ኛው የግንቦት 20 በዓል በተለያዩ አገራት እየተከበረ ነው

የመንግስት መስሪያ ቤቶች የተነደፉ ዕቅዶችን ተግባራዊ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንዲሰሩ ተጠየቀ

የፌደራሊዝም ስርዓቱ ዜጎች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያሳድጉ እድል የሰጠ መሆኑን ምሁራን ገለጸ

ዶክተር ቴድሮስ አድሓኖም ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ

ምርጫ ምርጫ

Back

የ5ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመጨረሻ ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል

ሰኔ 14፣2007

የአምስተኛው ጠቅላላ ምርጫ የመጨረሻ ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እንደገለፀው ሁሉም የምርጫው ውጤት ከመላ ሃገሪቱ ሙሉ በሙሉ ተሰባስቦ ተጠናቋል።

በቅርቡ ሰኔ 7 ቀን 2007 ዓ.ም በደቡብ ክልል፣ በጊምቦ ጋወታ የምርጫ ክልል የተካሄደው የምርጫ ውጤትም ለቦርዱ ደርሷል።

በዚህ መሰረትም በአጠቃላይ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤት ከተወዳድሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አሸናፊው ይፋ ይሆናል።

በምርጫው ለመሳተፍ ከተመዘገበው 36 ነጥብ 8 ሚሊየን ህዝብ ውስጥ ምን ያህሉ እንደመረጠም በትክክል በዚሁ እለት ይታወቃል።

ቦርዱ ምርጫውን ተከትሎ ቀደም ብሎ በገለፀው ጊዜያዊ ውጤት መሰረት ከ547 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ መካከል 442ቱን ኢህአዴግና አጋር ድርጅቶቹ ማሸነፋቸው ይታወሳል ።

የመጨረሻው ውጤት ይፋ ሲደረግ የሁሉም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበር አሸናፊ ፓርቲዎችና በጊዜያዊነት ውጤታቸው ያልተገለፁ የክልል ምክር ቤት አሸናፊዎችም እንደሚታወቁ ተነግሯል።

ምንጭ፡-ኤፍ.ቢ.ሲ