Back

የሞባይል ካርድ እጥረት በመከሰቱ የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች መቸገራቸውን ገለፁ

መስከረም 02፣2010

በሀገሪቱ የሞባይል ካርድ እጥረት በመከሰቱ የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች መቸገራቸውን ገለፁ፡፡

በሀገሪቷ አንዳንድ አካባቢዎች ከ10 ብር ጀምሮ ይሸጡ የነበሩ የሞባይል ካርዶች ላይ እጥረት መኖሩን አቢሲ ለማረጋጥ ችሏል፡፡

በዚህም የሞባይል ተጠቃሚዎች የባለ 100 ብር፣ባለ 50 ብር፣ባለ 25 ብር እና ባለ15 ብርና የ10 ብር የሞባይል ካዶች በገበያ ላይ አለመገኘታቸው ለችግር መዳረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ የኢትዮ-ቴሌኮም የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አብዱራሂም አህመድ በተለይ ለኢቢሲ እንደተናገሩት የሞባይል ካርድ እጥረቱ የተከሰተው በዋናነት ከ15 ብር በላይ ዋጋ ባላቸው ካርዶች ላይ ነው፡፡  

የኢቢሲ ሪፖርተሮች በኦሮሚያ፣ በደቡብና አማራ ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አባባ ክልሎች ተዘዋውረው ችግሩ መኖሩን አረጋግጠዋል፡፡        

የሞባይል እጥረቱ የተከሰተውም ካርዶቹ ከውጭ ሀገር ስለሚገቡ የውጭ አስመጪ ኩባንያዎች ለኤርፖርት ጉምሩክ ማቅረብ የነበረባቸውን ሰነድ ባለማሟላታቸው ካርዶቹ በወቅቱ ሀገር ውስጥ ባለመግባታቸው  ነው ብለዋል፡፡  

አሁን ላይ ግን ይህ ችግር በመቀረፉ የሞባይል ካርዶቹ  ከዛሬ ጀምሮ በሳምንት ጊዜ ውስጥ ለተጠቃሚዎች እንደሚቀርብ አቶ አብዱራሂም ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም ተመሳሳይ እጥረቱ ዳግም እንዳይከሰት በኢትዮ-ቴሌኮም ሽያጭ ማዕከሎች የኤሌክትሮኒስ የሞባይል ካርድ ግብይት በማስፋፋት ተመሳሳይ ችግር እንዳይከሰት ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የሞባይል ካርዶች በሀገር ውስጥ የሚመረትበት መንገድ በቀጣይ ይመቻቻል ሲሉም ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

የሞባይክ ካርድ እጥረቱን ተከትሎ በአንዳንድ አካባቢዎች ከካርዶች መሸጫ ዋጋ በላይ የሚሸጡ መኖራቸውንና ኢቢሲ ይህንንም ማረጋጡገጡን ለቀረበላቸው ጥያቄ ፣ይህን ድርጊት በሚፈፅሙ አካላት የኢትዮ ቴሌኮም እየተከታተለ ህጋዊና አስተዳራዊ እርምጃ እንደሚወስድ አመልክቷል፡፡ይህንንም ለማድረግ ኩባንያው በሚስጥርና በዘረጋው አሰራር ክትትል እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡     

ሪፖርተር፦ሰለሞን አብርሃ  


ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከዴንማርኩ አቻቸው ጋር ተወያዩ

የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በአካባቢው ነዋሪዎች ጥበቃ እየተደረገለት ነው

የመምህራኑ ውይይት በትምህርትና ሥልጠናው ዘርፍ የተያዙ ግቦችን በጋራ ለመፈፀም ያስችላል:- ት/ ሚኒስቴር

የሱዳን ካራሪ ዩኒቨርስቲ ለኢታማዦር ሹም ጀኔራል ሳሞራ የኑስ የክብር ዶክትሬት ሰጠ

የኦማን ሞተር ሳይክለኞች በኢትዮጵያ ባለው ሰላም መደነቃቸውን ገለፁ

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት መዳረሻ ከሆኑ አምስት የአፍሪካ አገራት አንዷ ናት-ራንድ መርቻንት ባንክ

ለኢትዮጵያ ከተሞች ዘመናዊ የመሬት መረጃ ምዝገባ የሚረዳ የሥልጠናና የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

በኦሮሚያ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ የተከሰተው ግጭት የሁለቱ ህዝቦች እሴት የሚገልፅ አይደለም:- የግጭቱ ተፈናቃዮች

ደኢህዴን በመልካም አስተዳደርና በወጣቶች ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታወቀ