Back

በአቶ አለማየሁ ጉጆ ስም 16 ግለሰቦች የተካተቱበት የሙስና ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ሊመሰረት ነው

መስከረም 03፣2010

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር በዋሉት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ኤዴታ በነበሩት አቶ አለማየሁ ጉጆ ስም 16 ግለሰቦች የተካተቱበት የምርመራ መዝገብ ተጠናቆ ክስ ሊመሰረት ነው፡፡

16 ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራው አጠናቆ ለአቃቤ ሕግ ማስረከቡን ያረጋገጠው ፖሊስ፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ የነበሩት አቶ ደጉ ላቀውም በዚሁ መዝገብ እንዲካተቱ ፍርድ ቤት አዟል፡፡

ክስ እንዲመሠረት ለመስከረም 12፣2010 ቀጠሮ በተያዘለት በዚህ መዝገብ ጳጉሜ 3/2ዐዐ9 በቁጥጥር ሥር የዋሉት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚንስትር ዴኤታ አማካሪ የነበሩት አቶ ደጉ ላቀው 17ኛ ሆነው እንዲካተቱ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት  ትላንት  ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ተጠርጣሪ ደጉ ላቀው የትራንስ ናሽናል የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂ ኩባንያ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር የነበረው የፕሮጀክት ውል መጠናቀቁን እያወቁ፣ ኩባንያው ከውጭ ከቀረጥ ነፃ ስምንት ተሽከርካሪዎችን በመሥሪያ ቤቱ ስም እንዲገቡ በማድረግ መንግሥትን 1ዐ ነጥብ 5 ሚሊዬን ብር እንዲያጣ አድርገዋል በሚል የሙስና ወንጀለ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡

የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ የሆኑት አትክልት ተስፋዬ 2ዐ ሚሊዬን ብር የሚገመት ጠጠርና ብረት ለየማነ ግርማይ ጠቅላላ ተቋራጭ በማዋስና ሳይመልስ በመቅረቱ ባደረሱት ጉዳት ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡

አቶ አትክልት ተስፋዬ ጉዳያቸው ከተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት  ከእነ አበበ ተስፋዬ የምርመራ መዝገብ ጋር ተጣምሮ እንዲቀርብለት ፍርድ ቤት ትዕዛዙን ሰጥቷል፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ፕሮጀክት ፅሕፈት ቤት ዋና ሥራ አሰኪያጅ በነበሩት ግለሰብ ስም ሲካሄድ የነበረው ምርመራ ለመስከረም 5፣2010 ክስ እንደቀርብበት ችሎቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡

ሪፖርተር፡‑ አባይነህ ጥላሁን

 

 


ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከዴንማርኩ አቻቸው ጋር ተወያዩ

የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በአካባቢው ነዋሪዎች ጥበቃ እየተደረገለት ነው

የመምህራኑ ውይይት በትምህርትና ሥልጠናው ዘርፍ የተያዙ ግቦችን በጋራ ለመፈፀም ያስችላል:- ት/ ሚኒስቴር

የሱዳን ካራሪ ዩኒቨርስቲ ለኢታማዦር ሹም ጀኔራል ሳሞራ የኑስ የክብር ዶክትሬት ሰጠ

የኦማን ሞተር ሳይክለኞች በኢትዮጵያ ባለው ሰላም መደነቃቸውን ገለፁ

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት መዳረሻ ከሆኑ አምስት የአፍሪካ አገራት አንዷ ናት-ራንድ መርቻንት ባንክ

ለኢትዮጵያ ከተሞች ዘመናዊ የመሬት መረጃ ምዝገባ የሚረዳ የሥልጠናና የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

በኦሮሚያ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ የተከሰተው ግጭት የሁለቱ ህዝቦች እሴት የሚገልፅ አይደለም:- የግጭቱ ተፈናቃዮች

ደኢህዴን በመልካም አስተዳደርና በወጣቶች ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታወቀ