Back

ሮጀር ፌደረል የምግዜውም ምርጥ ነው ሴሪና ዊልያምስ

ታህሳስ 24፣ 2011 ዓ.ም

በሆፕ ማን ዋንጫ ሴሪና ዊልያምስ እና ሮጀር ፌደረልን በባላንጣነት ያገናኘው የሁለትዮሽ የቴኒስ ጨዋታ በሮጀር ፌደረል አሸናፊነት መጠናቀቁን ተከትሎ ሮጀር ፌደረል የምንግዜውም ምርጥ ነው ስትል ሴሪና ዊልያምስ ተናገረች፡፡

ሴሪና ዊልያምስ ከፍራንሲስ ቲያፎ ጋር በመጣመር እና ሮጀር ፌደረል ከቤሊንዳ ቤንቺ ጋር ከመጣመር ባደሩት ጨዋታ የእነ ፌደረል ቡድን 4ለ2 እና 4ለ3 በማሸነፍ ጨዋታቸውን ጨርሰዋል፡፡

ሮጀር ፌደረል በበኩሉ ሴሪና ዊልያምስ ጨዋታው እንዲካሄድ ስላደገቸው ጥረት አመስግኖ ጨዋታው አዝናኝ እንደነበር ተናግሯል፡፡

ምንጭ ቢዝነስ ኢንሳይደር