Back

ፋሲል ከነማ ድል ሲቀናው ፣መከላከያ ከስሁል ሽሬ ጋር በአቻ ውጤት ተለያየ

ጥር 10፣2011

ፋሲል ከነማ ድል ሲቀናው ፣መከላከያ ከስሁል ሽሬ ጋር በአቻ ውጤት ተለያየ፡፡

ዛሬ በተካሄዱ ሁለት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሊግ ጨዋታዎች ፋሲል ከተማ ወላይታ ድቻን ለ1 ለባዶ ሲረታ፣መከላከያ ደግሞ ከስሁል ሽሬ ጋር 2ለ2 አቻ በሆነ ውጤት አጠናቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ነው ውጤቶቹ የተመዘገቡት፡፡

ጎንደር ላይ በአፄ ፋሲለደስ ስታድየም ፋሲል ከነማ ከወላይታ ዲቻ ጋር  ያደረጉት ጨዋታ  ያሬድ ባዬ በ86ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠራት ግብ 1ለ0 ማሸነፍ ችሏል፡፡

ለመከላከያ ደግሞ ፍፁም ገ/ማርያም ሁለቱን ግቦች ሲያሰቆጥር፣ ለስሁል ሽሬ ልደቱ ለማ እና ኪዳኔ አሰፋ አንድ አንድ ግብ በስማቸው አስመዝግበዋል፡፡

በላሉ ኢታላ

ፎቶ ፡- ከፋሲል ከነማ ክለብ