Back

ዶናልድ ትራንፕ ለታይገር ውድስ የነፃነት ክብር ሜዳልያ አበረከቱ

ሚያዝያ 8 2011 ዓ.ም

በሳምንቱ መጨረሻ ታዋቂው የጎልፍ ተጫዋች ታይገር ውድስ ለአምስተኛ ግዜ አሸናፊ የሆነበትን ውጤት ባስመዘገበበት ማግስት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራንፕ የነፃነት የክብር ሜዳልያ ሽልማት አበርክተውለታል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ሰሞኑን በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት ታይገር ውድስ የተቀበለው ሽልማት  በጎልፍ ማሰተር ውድድር ግንባር ቀደም በመሆኑ እንደሆነ አሰታውቀዋል፡፡

ታይገር ውድስ ሰሞኑን ያሰመዘገበው ውጤት ከ14 ዓመት ጉዳት ቆይታ በኃላ የተመዘገበ እንደሆነም ሲንን ዘግቧል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራንፕ ለበርካታ ስፖርተኞች ተመሳሳይ ሽልማት ማበርከታቸውን ሲንን በዘገባው አስታውቋል፡፡

ምንጭ ሲ.ኤን.ኤን