Back

በአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ሴኔጋልና ናይጄሪያ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አለፉ

ሀምሌ4 /2011

በአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ በሩብ ፍፃሜ ትላንት ደቡብ አፍሪካን የገጠመችው ናይጄሪያ 2ለ1 በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ተቀላቅላለች፡፡

ለናይጄሪያ ቹክዉንዜና ትሩት ኤኮንግ አንድ አንድ ግቦችን ሲያስቆጥሩ ለደቡብ አፍሪካ ብቸኛዋን ግብ  ዙንጉ ማስቆጠር ችሏል፡፡

በተመሳሳይ ሴንጋል ጉዬ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ቤኒን 1ለ0 በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፍ ችላለች፡፡

ቀሪ የሩብ ፍፃሜ ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ የሚደረጉ ሲሆን አይቮሪኮስት ከአልጄሪያ  እንዲሁም ማዳጋስካር ከቱኒዚያ ጋር ይጫወታሉ፡፡

በግማሽ ፍፃሜው የአይቮሪኮስትና የአልጄሪያ አሸናፊ  ከናይጄሪያ  እንዲሁም የማዳጋስካርና የቱኒዚያ አሸናፊ  ከሴኔጋል ጋር የፊታችን እሁድ የሚጫወቱ ይሆናል፡፡  

ምንጭ፡- ካፍ